እምነት፣ይቅርታና፣ ቤተሰብ

በማቴዎስ ወንጌል ውስጥ የምንመለከተው ነገር ኢየሱስ በተለያዩ ተረቶች፣ ትምህርቶችና ምሳሌዎች እንዳስተማረ ነው፡፡ እርሱ “ለሚያምን ሁሉም ነገር ይቻላል” በማለት ስለእምነት አስፈላጊነት አስተማረ፡፡ ኢየሱስ በተደጋጋሚ ስለይቅርታ አስተምሯል፡፡ ይቅር ስለተባልን እኛም በቋሚነት ይቅር ማለት አለብን፡፡ ጋብቻ ቅዱስ ቃል ኪዳን ስለሆነ መፍረስ እንደሌለበት አበክሮ በመናገር ስለ ጋብቻና ፍቺ ኢየሱስ አስተማረ፡