ስብከት አስር ጨው እና ብርሃን

እውነተኛ ደቀ መዛሙርት መደበቅ የማይችሉት እውነት ኢየሱስ እነርሱን የባህል ለውጥ እንዲያመጡ እንደሚጠቀምባቸው ነው፡፡ የእርሱ ደቀ መዛሙርት በተራራ ላይ እንዳለች ከተማና በመቅረዝ ላይ እንዳለ ሻማ ናቸው፡፡ በጨለማ ለሚገኙ እጅግ በርካታ ሰዎች ብቸኛ ብርሃን ክርስቲያኖች ብቻ ናቸው፡፡ የእርሱ ደቀ መዛሙርት ጨው እና ብርሃን የመሆን ሚናቸውን ካልተወጡ ማንም ሊወጣው አይችልም፡፡ደቀ መዛሙርት ወደ አለም የተላኩት የእግዚአብሔርን መፍትሄ ሁሉም ሰው እንዲያንጸባርቁ ነው፡፡