ስብከት ስምንት የተሰዯደ የሰሊም መሌክተኞች እና ተስፋዎች

“ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፣ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና፡፡” የሚያስታርቁ ብፁዓን የሚለውን ተከትሎ ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው የሚለው መጠቀሱ ምክንያት አለው፡፡ እነዚያ የእርቅ አገልግሎት አገልጋዮች ብዙ ጊዜ መከራን ይቀበላሉ፣ ሕይወታቸውንም የሚያጡበት ጊዜ አለ፣ ምክንያቱም እነርሱ ራሳቸውን የኢየሱስ ወገን ስላደረጉ ነው፡፡ እውነተኛ ደቀ መዛሙርት፣ በኢየሱስ የሚኖሩ፣ “የብፁዓን” ባሕርይ ያላቸው፣ ሰዎች መሆን እንዳለባቸው እንዲሆኑ በመልካም ሥነ ምግባር ሰዎችን የሚሞግቱ ብዙ ጊዜ ለኢየሱስ መከራን ይቀበላሉ፡፡