ስብከት ዘጠኝ ባህሌ እና ባህሪይ

ብፁዓን የኢየሱስ የተራራው ስብከት መሠረታዊ ሐሳቦች ናቸው፡፡ እነዚህ ብፁዓን ዓለምን የሚለውጡትን መልካም ባሕርያት የሚገልፁ ናቸው፡፡ ቀጥሎ ኢየሱስ የእርሱ ደቀ መዛሙርት የሚኖሩበትን ባህልና ሕብረተሰብ እንዲለውጡ ማብራሪያና የትግበራን ትምህርት ሰጥቷል፡፡ ደቀ መዛሙርት ክርስቶስን በሚመስል ባሕርይ የዓለምን ሕዝብ ሲያገለግሉ፣ እነርሱ ሥጋን ከመበስበስ እንደሚጠብቅ ጨው፣ የእነርሱ ተፅዕኖ ዓለምን ከመጥፋት ያድናል፣ እነርሱም ጠቃሚ የሆኑ ኢየሱስ የሚጠቀምባቸው አስፈላጊ ሰዎች ይሆናሉ፡፡