ስብከት ሰባት የእርቅ አገሌግልት

ሰባተኛው ብፁዓን (የሚያስታርቁ ብፁዓን ናቸው፣ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና) የሚናገረው የእግዚአብሔር መፍትሄ ተልዕኮ አካል ለሆኑት ነው፡፡ የሰው ልጆች ከእግዚአብሔር ተለይተዋል፡፡ እና ከእግዚአብሔር ጋር ከታረቅን - ከእርሱ ጋር ያለን ግንኙነት ትክክለኛ ከሆነ - ሌሎችን ከእርሱ ጋር እንድናስታርቅ እግዚአብሔር ይጠቀምብናል፡፡ እንዲሁም እርሱ እኛ እንድንታረቅና ሌሎችም እንዲታረቁ ይረዳቸዋል፡፡