ስብከት አምስት የተሇየ ፅዴቅ

ለጽድቅ መራብና መጠማት ትክክለኛን ነገር ለማወቅ በጥልቅ ፍላጎት መፈለግ ነው፡፡ እንዴት እንደምታደርጉና ምን እንደምታደርጉት ለእግዚአብሔር አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ እኛ የተጠራነው ትክክለኛውን ነገር እንድናደርግ ነው እንጂ ምቹ ነገሮችን እንድናደርግ አይደለም፡፡ ብፁዓን በሚለው ትምህርት ውስጥ ንድፍን እንመለከታለን፡፡ እነዚህ ብፁዓን በሚለው ትምህርቶች ውስጥ ሁሉም የቀረቡት ጥንድ ጥንድ ሆነው፡፡ እኛ የምናዝነው በመንፈስ ድሆች እየሆንን ነው፣ እኛ የዋሆች ስንሆን ለጽድቅ እንራባለን እንጠማለን፡፡ የተሰጠን ተስፋ ሙሉ በሙሉ እንደምንሞላ ነው፡፡