ስብከት ስዴስት የፍቅር ሌብ

“የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፣ ይማራሉና፡፡ ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፣ እግዚአብሔርን ያዩታልና፡፡” “ምሕረት” ሚለው ቃል “ቅድመ ሁኔታ የሌለበት ፍቅር” ማለት ነው፡፡ የዚህ ዓይነት ፍቅር ደቀ መዛሙርቱ የእግዚአብሔርን ፍቅር ለሌሎች ማስተላለፍ የሚችሉ እንዲሆኑ የሚያስችላቸው ነው፡፡ እኛ የምሕረት ሰዎች ስንሆን የእኛ ፍላጎት ጥያቄ ላይ ይወድቃል ምክንያቱም ቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ፍቅርን ለመረዳት ከባድ ስለሆነ ነው፣ በተለይም የዚህን ዓይነት ፍቅር አይተው ለማያውቁ ሰዎች፡፡ እግዚአብሔር እኛን በወደደበት ፍቅር እኛም ሌሎችን ስንወድድ ፍላጎታችን ንፁህ ይሆናል፡፡