ስብከት አንዴ የተራራው ሊይ ስብከት አውዴ

በጣም አስፈላጊ በሆነው የተራራው ስብከት ኢየሱስ በገሊላ በሚገኝ ተራራ ላይ የእርሱ ደቀ መዛሙርት ነን የሚሉትን ሰዎች የሞገተበት፣ ደቀ መዛሙርቱን በእግዚአብሔር ፍቅርና በዓለም ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን በሚያሰቃይ ሕመም መካከል ስልታዊ በሆነ መንገድ ያስቀመጠበት ነው፡፡ እርሱ የራሱን ደቀ መዛሙርት ከእርሱ ጋር አብረው እንዲሰሩና የእርሱ ፍቅር አስተላላፊዎች እንዲሆኑ ሞገታቸው፡፡ እርሱ የተራራውን ስብከት ያጠናቀቀው አድማጮቹ ለእርሱ የተሰጡ እንዲሆኑና 12ቱን ሰዎች ሐዋርያት፣ ወይም “የተላኩ” ብሎ በመመደብ ሲሆን እነዚህ ሰዎች ለኢየሱስ ኖረው ለኢየሱስ የሞቱ ናቸው፡፡