የክርስትና ህይወት መርሖዎች

ይህ ትምህርት መሰረታዊ የሆኑ የክርስትና ርእሶች ላይ በስፋት ያስትምራል። ይህ በተለይ ለአዳዲስ አማኞች በጣም ጠቃሚ ነዉ። በሁሉም መልኩ ለእየሱስ ክርስቶስ ስልጣን ይገዙ ዘንድ ያግዛቸዋል። በክርስትያናዊ ህይወት እንዲያድጉ እና መታዘዝን በህይወታቸዉ እንዲለማመዱ ይረዳቸዋል። ስለእግዚአብሄር እና ስለእግዚአብሄር ቃል ያላቸዉን እዉቀት ያዳብሩ ዘንድ ያግዛቸዋል። ሌሎችን በፍቅር ማገልገል ያስችላቸዋል። ቤተክርስቲያንን በወንጌላዊነት እና በደቀመዝሙርነት እንድትሰፋ ይረዳል።

የመንፈሳዊ አመራር መሰረቶች

የመንፈሳዊ አመራር መሰረቶች በተለይ ከአመራር ጋር የተያያዘ ትምህርትን ከክርስትያናዊ እይታ አንጻር እና አንድ ሰው መንፈሳዊ መሪነትን በተግባር የሚያከናውንባቸው የሕይወት መድረኮች ተመርኩዞ የሚሰጥ ነው። ለእዚህ ለመንፈሳዊ አመራር መሰረቶች ታሳቢ ተደራሾች ተደርገው የሚወሰዱት የክርስትና እምነት መሰረታዊ እውቀት እና ልምምድ ያላቸው እና በእምነቱ ውስጥ ሌሎችን መምራት የጀመሩ ክርስቲያኖች ናቸው። የመንፈሳዊ አመራር ልምምድ የሚደረገው በቤት ውስጥ፣ በስራ ቦታ፣ በትንንሽ ቡድኖች ውስጥ እና በደቀ መዝሙርነት ግንኙነቶች ውስጥ እና በቤተክርስቲያን ውስጥ በሚሰጡ መደበኛ ቦታዎች ላይ ማለትም በአስተማሪነት፣ በፓስተርነት፣ በሽማግሌነት ወይንም በዲያቆንነት ውስጥ ሊሆን ይችላል።