የኢየሱስ ውልደት፦ ሉቃስ 1-2

ስለሉቃስ ወንጌል ከሚያስተምረው ባለ አምስት ክፍል ተከታታይ ትምህርት የመጀመሪያው። በኢየሱስ ውልደት ዙሪያ ያሉትን አስደናቂ ኩነቶች እንዳስሳለን። የኢየሱስ ቤተሰብ በእስራኤላውያን ማኅበረሰብ መካከል የነበራቸው አነስተኛ ማህበራዊ ደረጃ፣ እንዲሁም ደግሞ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃቸው በኢየሱስ መንግሥት ዘንድ ነገሮች ሁሉ የተገላቢጦሽ እንደሆኑ ያመላክታል። #BibleProject #ሉቃስ …ንባብ ጨምር

ሻሎም - ሰላም

“ሰላም" በአማርኛ የተለመደና ለተለያዩ ሰዎች የተለያየ ትርጉሙ ያለው ቃል ነው። ቃሉ በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ የግጭት አለመኖርን ብቻ ሳይሆን የሌላ ነገር መኖርን ያመላክታል። በዚህ ቪድዮ፣ መጽሃፍ ቅዱስ ስለሰላም ወይም ሻሎም የሚያስተምረውን ጥልቅ ሐሳብ እንመረምራለን። #BibleProject #ሰላም #Shalom

ተስፋ

በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ፣ ተስፋ ማድረግ ከተስፈኝነት በጣም ይለያል! መጽሃፍ ቅዱሳዊው ተስፋ፣ ነገ ከዛሬ ይሻላል ለሚለው እምነት መሰረት የሚያደርገው የእግዚአብሔርን ማንነት ብቻ እንደሆነ በዚህ ቪድዮ እንመለከታለን። #BibleProject #ተስፋ #Hope

ደስታ

በዚህ ቪድዮ የእግዚአብሔር ህዝብ እንዲላበሰው ስለተጠራበት በአይነቱ ልዩ ስለሆነው ደስታ እንነጋገራለን። ይህ ደስታ ከስሜት ያለፈ ነው፤ ይልቁንም እግዚአብሔር የተናገረውን እንደሚፈጽም ለማመን መምረጥ ነው። #BibleProject #ደስታ #Joy

አጋፔ - ፍቅር

በእኛ አጠቃቀም “ፍቅር” የሚለው ቃል በአብዛኛው የሚያመለክተው በሰው ላይ የሚከሰትን ስሜት ስለሆነ፣ በቋንቋችን ውስጥ በጣም ግራ-አጋቢ ከሆኑት ቃላት አንዱ ሆኗል። በአዲስ ኪዳን ውስጥ ግን “ፍቅር” ወይም “አጋፔ” የሚያመለክተው ስሜትን ሳይሆን ከሰዎች ጋር ያለን መስተጋብር እንደሆነ ጌታ ኢየሱስ አስተምሯል። ይህ ማለት ፍቅር ምላሽ ሳይጠብቁ የሌሎችን በጎነት መፈለግ ማለት ነው። #BibleProject #ፍቅር #Agape