My360 Helper


የከተማ ፋይዳ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ (እና እግዚአብሔር ለከተማ ያለው እቅድ)

በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ በቃየን ከተገነባችው የመጀመሪያዋ ከተማ ጀምሮ፣ በአዲሱ ፍጥረት ውስጥ የመጨረሻዋ የአትክልት ከተማ እስከሆነችው እስከ ሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም ድረስ የከተማን ጭብጥ ይመርምሩ። በዚህ ቪዲዮ የሚከተሉትን ይማራሉ፦ - ከተማን ከተማ የሚያደርገው ምን እንደ ሆነ - የመጀመሪያው ከተማ ለምን እንደ ተሠራ - የባቢሎን እና የእግዚአብሔር ከተማ ያላቸው ተቃርኗዊ ሥነ ምግባር - እግዚአብሔር የአትክልት ስፍራውን ወደ ከተማዋ ለማምጣት ያለው ያልተጠበቀ ዕቅድ - ሰማያዊቷ ከተማ ወደ ምድር ስትመጣ ምን እንደምትመስል መጽሐፍ ቅዱስ …ንባብ ጨምር

የሕይወት ዛፍ

በመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያዎቹ ገጾች ውስጥ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ስጦታ ሰጥቷቸዋል፤ ይህን ሥጦታ ሰዎች በጥፋታቸው ምክንያት ወዲያውኑ ያጡት ሲሆን፣ ስጦታውም የሕይወት ዛፍን በመብላት የሚገኝ የዘላለም ሕይወት ነበር። በዚህ ቪዲዮ፣ የዚህን ብርቱ መልእክት ያለውን ምስል ትርጕም እና በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ የተቀደሱ ዛፎች የሚጫወቱትን ቍልፍ ሚና እንመረምራለን። ይህ ምስል ለሰው ልጆች ሁሉ አዲስ የሕይወት ዛፍ ይሆን ዘንድ በዕንጨት ላይ ወደ ሞተው ኢየሱስ የሚመራን ነው። #BibleProject #Bible #የሕይወት ዛፍ የቪዲዮ ምስጋናዎች የአማርኛ ፕሮዳክሽን ቡድን BETE-SEMAY Creative Media Addis Ababa, Ethiopia ኦሪጅናል የእንግሊዘኛ ይዘትና ፕሮዳክሽን BibleProject ፖርትላንድ፣ ኦሬገን፣ ዩ.ኤስ.ኤ

ፍትሕ

በዛሬው ዓለም ውስጥ ፍትሕ እጅግ ተፈላጊ እና አጨቃጫቂ ርእሰ ጕዳይ ነው። ነገር ግን ፍትሕ ምንድን ነው? ብይን የሚሰጠውስ ማን ነው? በዚህ ቪዲዮ፣ የመጽሐፍ ቅዱስን የፍትሕ ጭብጥ እንመረምራለን፤ እንዲሁም ፍትሕ በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ ሥር የሰደደ ፅንሰ ዐሳብና ወደ ኢየሱስ የሚመራን መሆኑን እንቃኛለን። #BibleProject #Bible #ፍትሕ

ቅድስና

በዚህ ቪዲዮ የእግዚአብሔር ቅድስና በሰው ልጆች ላይ ስለሚያመጣው ተቃርኖ እንመረምራለን። እግዚአብሔር ፍጹም የተለየ፣ የእውነት ሁሉ ፈጣሪ እና የመልካምነት ሁሉ ደራሲ ነው። ሆኖም ግን፣ ይህ የእግዚአብሔር መልካምነት ለሟች እና ለምግባረ ብልሹ ሰዎች አደገኛ ሊሆን ይችላል። በመጨረሻም፣ ይህ ተቃርኖ የተፈታው ፍጥረቱን ለመፈወስ በመጣውና የእግዚአብሔር ቅድስና መገለጫ በሆነው በኢየሱስ ነው። #BibleProject #Bible #ቅድስና

የእግዚአብሔር አምሳል

ይህ በእግዚአብሔር አምሳል ላይ ትኵረቱን ያደረገው ቪዲዮ፣ ምድርን እና በውስጧ ያሉትን እንዲያለሙ እና ወደ አዲስ አድማስ እንዲወስዷቸው ተልእኮ የተሰጣቸው ከእግዚአብሔር ጋር ዐብረው የሚገዙ ሰዎችን ዕሳብ ይመረምራል። ይህ የከበረ ጥሪ በራስ ወዳድነታችን እና በክፋታችን የተሸረሸረው እንዴት ነው? ኢየሱስ በሕይወቱ፣ በሞቱና በትንሣኤው አማካኝነት ሰው ለመሆን የሚያስችለንን አዲስ መንገድ የከፈተልንስ እንዴት ነው? #BibleProject #Bible #የእግዚአብሔር አምሳል

መንፈስ ቅዱስ

በዚህ ቪዲዮ፣ “መንፈስ” የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ፅንሰ ዐሳብ ቀዳሚ ፍቺ እንመረምራለን፤ በተጨማሪም የእግዚአብሔር መንፈስ በፍጥረት ሁሉ ውስጥ መገኘቱ ምን ማለት እንደ ሆነ እንመለከታለን። በመጨረሻም፣ መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ በኩል ተገለጦ አዲስ ፍጥረትን ለማምጣት ወደ ተከታዮቹ ሕይወት ተልኳል። #BibleProject #Bible #መንፈስ ቅዱስ

የስደት መንገድ

የኢየሱስ ተከታዮች ለእግዚአብሔር መንግሥት ሙሉ በሙሉ ታማኝ መሆን ከፈለጉ፣ በዘመናቸው ካሉ መንግሥታትና የሥልጣን መዋቅሮች ጋር እንዴት ያለ ግንኙነት ሊኖራቸው ይገባል? በዚህ ቪዲዮ ዳንኤል እና ጓደኞቹ በባቢሎን ግዞት ሳሉ ያሳለፉት ተሞክሮ፣ ውጥረቱን ለመመርመር የሚሰጠንን ጥበብ እንመለከታለን። በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኢየሱስን መከተል ማለት የስደትን መንገድ መማር ማለት ነው። #BibleProject #Bible #የስደት መንገድ

ዘላለማዊ ሕይወት

ኢየሱስ ለሰዎች የዘላለም ሕይወትን ይሰጣል፤ ሆኖም ግን የዘላለም ሕይወት ምን ማለት ነው? አሁን እና በሚመጣው ዘመን ወደ እግዚአብሔር ሕይወት የሚጋብዘንን የዚህን ሐረግ ፍቺ ይመርምሩ። #BibleProject #Bible #ዘላለማዊ ሕይወት

የሰው ልጅ

“ክርስቶስ” የኢየሱስ የመጨረሻ ስም ወይም ለራሱ የሰጠው የማዕረግ ስም የሚመስልዎ ከሆነ፣ እንደገና ቈም ብለው ማሰብ ይኖርብዎታል! ኢየሱስ ራሱን ለመግለጽ ብዙውን ጊዜ ይጠቀምበት የነበረው ስም፣ “የሰው ልጅ” የሚል ነው። በዚህ ቪዲዮ፣ የዚህን አስደናቂ መጠሪያ ሐረግ ትርጕም እንመረምራለን፤ ይህም እንዴት ወደ ትልቁ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ እንዴት እንደሚመራን እንመለከታለን። #BibleProject #Bible #የሰው ልጅ

የጌታ ቀን

እግዚአብሔር በዓለም ላይ ሰዎች ለሚፈጽሟቸው እኩይ ተግባራት ግድ ይለዋልን? ግድ የሚለው ከሆነ ምን እያደረገ ነው? በዚህ “የጌታ ቀን” በተሰኘ ቪዲዮ፣ እግዚአብሔር የሰውን እኩይ ተግባር የሚጋፈጥባቸውን የተለያዩ መንገዶች፣ እንዲሁም ከዚህ እኩይ ጀርባ ያለውን ጥልቅ መንፈሳዊ ክፋት እንመረምራለን። በመጨረሻ፣ ኢየሱስ ይህን የታሪክ ሴራ እንዴት ወደ ፍጻሜ እንዳመጣው እና እኩዩ እንዲያሸንፈው በመፍቀድ፣ እንዴት እንደረታው እንመለከታለን። #BibleProject #Bible #የጌታ ቀን

የመንግሥቱ ወንጌል

በዚህ ቪዲዮ “ወንጌል” ስለተሰኘው ቃል አመጣጥና፣ ቃሉ የብሉይ ኪዳንን ታሪክ ከኢየሱስ ታሪክና ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ካወጀው ታሪክ ጋር እንዴት እንደሚያያዝ እንመለከታለን። ኢየሱስ የእግዚአብሔርን አገዛዝ እና ንግሥና ወደዚህ ዓለም ያመጣው ባልተጠበቀ መንገድ ነው፤ ይህም እንዲሰሙ ከሚመኙት እጅግ የላቀው የምሥራች ነው። #BibleProject #Bible #የመንግሥቱ ወንጌል